Fana: At a Speed of Life!

በሰብል ከተሸፈነ 6 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር መሬት ውስጥ ከ4 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ የተዘራ ሰብል ተሰብስቧል- የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2013 ዓ.ም በሰብል ከተሸፈነ 6 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር መሬት ውስጥ ከ4 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ የተዘራ ሰብል መሰብሰቡን የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ኃይሉ አዱኛ አስታወቁ፡፡
የአገርን ሉዓላዊነት ከማስጠበቅ ጎን ለጎን ምጣኔ ሃብቱ እንዳይዋዥቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው፥ በክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች ላይ የመስኖ ሥራ ተጠናክሮ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በተያዘው የበጀት ዓመትም መጠነ ሰፊ የመስኖ ሥራዎችን በመስራት የአገሪቱ ኢኮኖሚ ሚዛኑን ጠብቆ እንዲጓዝ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
ድርቅ በተከሰተባቸው የክልሉ አካባቢዎች ከ100 ሺህ በላይ ኩንታል እህል ድጋፍ መደረጉንም አብራርተዋል።
በአመርቲ ተስፋዬ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.