Fana: At a Speed of Life!

በሱዳን የመስቀል በዓል በድምቀት ተከበረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የመስቀል በዓል በሱዳን ካርቱም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ደብረ-ሠላም መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን የሃይማኖት አባቶችና የዕምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ-ሥርዓቶች በድምቀት ተከብሯል፡፡

በስነ ሥርዓቱ ላይ በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልእክታቸውም÷ የመስቀል በዓል ለኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት የተመዘገበ ለመላው የሠው ልጆች ሃብት እንደሆነ፣ ሃገራችን ኢትዮጵያ የበርካታ የታሪክ እና የተፈጥሮ ሃብቶች ባለጸጋ እንደሆነች፣ ሆኖም ህዝቧ ከድህነትና ከስደት ያልተላቀቀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ጨምረውም÷ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሃብቷን አልምታ ከድህነት እንዳትወጣ በተለያየ ጊዜ ከውስጥና ከውጭ የሚነሱ ጠላቶች ፈተና እንደሆኑባት፣ በአሁኑ ወቅት ዘርን እንደ መቀስቀሻ የሚጠቀሙ ሃይሎች ጠባብ የቡድን ፍላጎታቸውን ለማሟላት ሕዝባችንን እርስ በእርስ ለማባላትና ሃገር ለማፍረስ እየሰሩ መሆኑን፣ ከዚህ አንጻር ኢትዮጵያዊያን በዘርና በሃይማኖት ሳይለያዩ አንድ ሆነው ለሃገራቸው ሠላምና አንድነት በጋራ መቆም እንደሚገባቸው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘገቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.