Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ  ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ልዑካን  በክልሉ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ልማት እንቅስቃሴዎችን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ  ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ልዑካን በክልሉ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ልማት እንቅስቃሴዎችን እና መሰረተ ልማቶችን ጎብኝቷል፡፡

በጉብኝቱ በዘርፉ ካሉ የኢንቨስትመንት መሰረተ ልማቶች አንዱ የሆነውን የይርጋለም የተቀናጀ አግሮ ኢንደስትሪ ፓርክ የተመለከቱ ሲሆን÷በዚህም በፓርኩ ውስጥ እየሰሩ ያሉ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ጎብኝተዋል፡፡

ፓርኩ በአጭር ጊዜ ውስጥ በዘርፉ እያሳየ ያለው አፈጻጸም አበረታች መሆኑ በጉብኝቱ ወቅት መገለጹን ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.