Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል 137 ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ የአስቸኳይ ጊዜ ክልከላ በነበረበት ጊዜ በድንገተኛ ፍተሻዎች የተለያዩ ተጠርጣሪዎችን መያዝ መቻሉን ተናግረዋል።
በዚህም በርካታ ጥይቶችና የጦር መሳሪያዎች እንዲሁም በግለሰቦች እጅ መኖር የሌለባቸው የጦር መሳሪያዎች መያዛቸውን ነው የተናገሩት።
ፍተሻውን የፈሩ ግለሰቦችም የእጅ ቦንቦችን በቆሻሻ ውስጥ ጥለው መገኘቱንም ገልጸዋል።
ተጠርጥረው በምርመራ ላይ የሚገኙ 137 ተጠርጣሪዎችም በምርመራ ቡድኑ አማካኝነት የማጣራት ስራ እየተደረገባቸው ነው ብለዋል።
ህዝቡ አካባቢውን ለመጠበቅ እያደረገ ያለው ተግባር የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው፥ በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
በብርሃኑ በጋሻው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.