Fana: At a Speed of Life!

በሳንፍራንሲስኮ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መንግስት ያካሄደውን የህግ ማስከበር ዘመቻ እና የህዳሴ ግድብን የሚደግፍ ሰልፍ አካሄዱ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ሳንፍራንሲስኮ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በትግራይ ክልል የተወሰደውን የህግ ማስከበር ዘመቻ እና የህዳሴ ግድብ ድርድርን በመደገፍ ሰልፍ አካሄዱ፡፡

ኢትዮጵያውያኑ ህወሓት በኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸመውን ግፍ አንስተዋል፡፡

በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ ሰብአዊ መብት ተቋማት እና በዋና ዋና የሚዲያ አውታሮች የሚሰሩ የቡድኑ አቀንቃኞች እና ደጋፊዎች ያለፈበት መንገድና ማህበራዊ ትስስር ገጾችን በመጠቀም የተሳሳቱ መረጃዎችን እያሰራጩ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

“በሚያሳዝን ሁኔታም እነዚህ መረጃዎች በተለይም ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ከማወናደበድና የተሳሳተ መረጃን ከመመገብ አንጻር ስኬታማ” መሆናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

ከዚህ በተቃራኒው ህወሓት በሰሜን ዕዝ ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ችግርና ቀውስ ሽፋን እንዳያገኝ ያደረጉበት መንገድም አሳዛኝ ነው ብለዋል ሰልፈኞቹ፡፡

ሰልፈኞቹ ታላላቅ ጋዜጦችና የሰብአዊ መብት ተቋማትን ጨምሮ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የትግራይ ክልልን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ በሚያቀርቡት ትንታኔ ወሳኝ እውነታዎች ሆን ብለው አለማቅረባቸው አግባብነት የሌለውና አሳዛኝ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ባነሱት ሃሳብ ግድቡ የኢትዮጵያውያን ህልውና መሆኑን አውስተዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም መንግስት የያዘውንና ግድቡን በፍትሃዊነትና በእኩልነት የመጠቀም መብት አካሄድን እንደሚደግፉም ገልጸዋል፡፡

የህዳሴው ግድብ መጠናቀቅ ከኢትዮጵያ እጣ ፈንታ ጋር የተቆራኘ መሆኑን በማንሳትም ለኢትዮጵያውያን ልዩነት ፈጣሪ ለሆነው ለዚህ ፕሮጀክት ስኬት ድጋፍ እንደሚያደርጉም አረጋግጠዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.