Fana: At a Speed of Life!

በሳውዲ አረቢያው ባለሀብት የተመራ የልኡካን ቡድን ጅግጅጋ ገባ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሳውዲ አረቢያው ባለሀብት ሼህ ሀምዛ የተመራ የልኡካን ቡድን ጅግጅጋ ከተማ ገብቷል።
የልኡካን ቡድኑ በገራድ ዊል ዋል አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የሶማሌ ክልል የፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሀሰን መሀመድ እና የተለያዩ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች አቀባበል አድርገዋል።
ባለሀብቶቹ በክልሉ የተገኙት በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት መሆኑ ተገልጿል።
በዚህም ከ 5 ሺህ እስከ 10 ሺህ ቤቶች ፣ በፀሀይ የሚሰራ የሶላር መገጣጠሚያና የመኪና መገጣጠሚያ ድርጅት ዘርፍ ላይ ኢንቨስት ለማድረግ መሆኑም ነው የተነገረው።
የነዳጅ ካምፓኒ ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ሳውዲ አረቢያዊው ሼህ ሀምዛ አብዲአዚዝ አል ሱኬሪያና የጊፍት ሪልዕስቴት ዋና ስራ ስራ አስኪያጅ አቶ ገብረእየሱስ ከክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ኡመር ጋር በመገኘት በክልሉ ኢንቨስትመንት ዙሪያ የምክክር አድርገዋል።
በዚሁ ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ የልኡካን ቡድኑ በክልሉ ለሚያከናውናቸው የኢንቨስትመንት ስራዎች የክልሉ ህዝብና መንግስት ከጎናቸው እንደሚቆም አረጋግጠዋል።
በክልሉ በሪል እስቴት መስክ ያሉ ክፍተቶችን ለመቅረፍ የባለ ሀብቶቹ ድርሻ የጎላ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን የመገጣጠሚያ ካምፓኒዎቹ መገንባትም በኢኮኖሚው ረገድ ያለው ሚና የጎላ እንደሆነም ተገልጿል።
ባለሀብቶቹ በደገሀሌ ተገኝተው የግብርና ልማቶችንና ካሁን በፊት በስጋ ኤክስፖርት ዘርፍ ይሰራ የነበረውን የጄሽ ካምፓኒ መጎብኘታቸውን ከሶማሌ ክልል ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.