Fana: At a Speed of Life!

በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚፈጸምን ጥቃት ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት በሚደረገው ጥረት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚፈጸምን ጥቃት ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት በሚደረገው ጥረት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ።

በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሴቶችና ህጻናት ፍትህ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት አዘጋጅነት በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚፈጸምን ጥቃት ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የተቀቋቋመው ብሄራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አካል የሆኑ ከፍተኛ አመራሮች ውይይት አካሂደዋል፡፡

በመድረኩ ብሄራዊ አስተባባሪ ኮሚቴው በተቀናጀና ዘርፈ ብዙ በሆነ መንገድ በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚፈጸምን ጥቃት ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት እንዲሁም የህጻናት ፍትህን ለማረጋገጥ የተቋቋመ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በውይይቱ ላይ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የብሄራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አካላት የሆኑ ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሴቶች፣ሕጻናትና ባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ እንቁ አስናቀ ባቀረቡት ጽሁፍ በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን የማስቀረትና መብታቸው እንዲከበር የመስራት ግዴታ የሁሉም ተቋማት ኃላፊነት ነው ተብሏል፡፡

በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን መከላከልም ሆነ ተፈጽሞ ሲገኝ የተሟላ አገልግሎት መስጠት በፍትህ ተቋማት ብቻ ሊፈጸም የማይችል መሆኑ በመድረኩ ላይ መጠቆሙን ከጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ያገኘኘው መረጃ ያመለክታል።

ተጎጂዎቹን በጥቃት ምክንያት ከሚደርስባቸው ዘርፈ ብዙ የጤና፣ የስነልቦና፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለማውጣትና መልሶ ለማቋቋም የሁሉም አካላት ቅንጅታዊ አሰራር አስፈላጊ ነው ተብሏል፡፡

ጥቃትን ከመከላከልና ምላሽ ከመስጠት አንፃር እስከ አሁን ባለው ሂደት በተናጠል የመንቀሳቀስ እንዲሁም ወጥነትና ቀጣይነት የጎደለው አላስፈላጊ ድግግሞሽ መስተዋሉም ተገምግሟል፡፡

በአጠቃላይ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች ስር የሰደዱ እና የተስፋፉ በመሆናቸው በተቀናጀና ዘርፈ ብዙ በሆነ መንገድ እርምጃዎችን መውሰድ በማስፈለጉ 19 አባል ተቋማትን ማለትም ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ የጤና ጠበቃ ሚኒስቴር፣ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣች ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የትምህርት ሚኒስቴርንና ሌሎች ተቋማትን የያዘ ብሄራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ ተገብቷልም ነው የተባለው፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.