Fana: At a Speed of Life!

በሴቶች የሴካፋ ዋንጫ ሉሲዎቹ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ሴቶች (ሴካፋ) ዋንጫ ሉሲዎቹ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል፡፡

ዛሬ በተደረገ የሴቶች የሴካፋ ዋንጫ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ሉሲዎቹ ደቡብ ሱዳንን 4 ለ 0 ረተዋል፡፡

በጨዋታው አረጋሽ ካልሳ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሃት – ትሪክ ስትሰራ ሎዛ አበራ አንደኛውን ጎል ማስቆጠር ችላለች፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ የምድብ 2 ሌላ ጨዋታ ደግሞ ታንዛኒያ ዛንዚባርን 12 ለ 0 በማሸነፏ ሉሲዎቹን በግብ ክፍያ በልጣ የምድቡ አንደኛ ስትሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ታንዛኒያን በመከተል ሁለተኛ ሆኖ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅሏል።

በግማሽ ፍፃሜው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከውድድሩ አስተናጋጅ ዩጋንዳ ጋር እንደሚጫወት የሶከር ኢትዮጵያ ዘገባ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.