Fana: At a Speed of Life!

በስድስት ወራት ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች ከ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ስድስት ወራት ወደ ውጭ ከተላኩ የተለያዩ ምርቶች ከ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ።

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ገቢው ቡና፣ ቅመማ ቅመም፣ ጥራጥሬ እና የቅባት እህሎች ገቢው ከተገኘባቸው ምርቶች መካከል እንደሚገኙበት ገልጸዋል፡፡

ገቢው ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም ከ224 ሚሊየን ዶላር በላይ ብልጫ ማሳየቱን አመላክተዋል።

ወደ ውጭ ከሚላኩ ምርትች በዓመት የሚገኘው ገቢ ከ3 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር መዝለል ያልቻለ ሲሆን፥ አሁን ያለው አቅምና አፈጻጸም ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ማሳካት አእንደማይቻልም ሚኒስትር ዲኤታው ተናግረዋል፡፡

በተለይም በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ተወዳዳሪ ለመሆንና የሀገሪቱን ጥቅም ለማስጠበቅ በወጭ ምርቶች ጥራትና ብዛት ላይ መስራት እንደሚገባ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.