Fana: At a Speed of Life!

በሶማሊያ ሞቃዲሾ በሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ላይ ተፈፀመ ጥቃት የ8 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሶማሊያ ሞቃዲሾ ከተማ በሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ላይ በተፈፀመ ጥቃት የ8 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።

ጥቃቱ በዛሬው እለት በሞቃዲሾ ከተማ ስታዲየም አቅራቢያ በሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ላይ ነው የተፈፀመው ተብሏል።

በጥቃቱም የ8 ሰዎች ህይወት ማለፉን እና 14 ሰዎች ላይ ደግሞ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት መድረሱን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አስታውቀዋል።

የጦር ካምፑ አዛዥ ሜጀር አብዱላሂ ሞሃመድ፥ በካምፑ ላይ ጥቃት መፈፀሙን አረጋግጠው፤ ጥቃቱም በተሽከርካሪ ላይ በተጠመደ ቦምብ ሳይፈፀም እንዳልቀረም ገልፀዋል።

በአሁኑ ሰዓትም ተጎጂዎችን በራሳቸው ትራንስፖርት ጭምር ወደ ጤና ተቋማት በማጓጓዝ ላይ እንደሆኑም ነው የተናገሩት።

በስርፋው የሚኖሪ የአይን እማኞችም ከቦምብ ጥቃቱ በኋላ የሶማሊያ ጦር ተኩስ መክፈቱን በመግለፅ፤ የተጎዱ ወታደሮች በተሽከርካሪ ተጭነው ሲወጡ መመልከታቸውንም ተናግረዋል።

የአምቡላንስ አገልግሎት የሚሰጡ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችም 8 አስከሬን እና 14 የተለያየ መጠን ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችን ከስፍራው ማንሳታቸውን ነው የሚናገሩት።

እስካሁንም በወታደራዊ ካምፑ ላይ ለተፈፀመው ጥቃት ኃላፊነት የወሰደ አካል አለመኖሩም ነው የተገለፀው።

ምንጭ፦ cgtn.com

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.