Fana: At a Speed of Life!

በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አዲስ ከተመረጡት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አብዱልፈታህ አብዱላሂ ሃሰን ከአዲሱ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በአገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸው ተገልጿል፡፡
ተመራጩ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት በትዊተር ገፃቸው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የደስታ መግለጫ ባስተላለፉት የምስጋና መልዕክት፥ የሁለቱን አገራት የሁለትዮሽ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
ባለፈው እሁድ የሶማሊያ ፓርላማ ሀሰን ሼክ ሞሀመድን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አድርጎ መምረጡ ይታወቃል።
ይህንንም ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለተመራጩ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም፥ ከፕሬዚዳንት ሞሀመድ ጋር ለኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የጋራ በሆኑ ሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተቀራርበው በጋራ እንደሚሰሩ እምነታቸውን መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.