Fana: At a Speed of Life!

በሶማሊያ ፓርላማ አቅራቢያ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት አራት ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ ፓርላማ አቅራቢያ በተፈጸመ ቦምብ ጥቃት በርካቶች ለህልፈት መዳረጋቸው ተነገረ።

በፍተሻ ጣቢያ አካባቢ በተፈጸመው ጥቃት እስካሁን አራት ሰዎች ሲሞቱ ከ10 ሰዎች በላይ መቁሰላቸው ተነግሯል።

ለጥቃቱ አልሸባብ ኃላፊነቱን ወስዷል።

በወቅቱ በተሽከርካሪ የተጫነን ፈንጂ የፍተሻ ጣቢያውን ለማሳለፍ ተሞክሮ እንደነበር ፖሊስ ገልጿል።

ይሁን እንጅ ይህ ባለመሳካቱ አጥፍቶ ጠፊው ጥቃቱን ማድረሱ ነው የተነገረው።

አልሸባብ ሞቃዲሾን በተደጋጋሚ የጥቃት ኢላማው አድርጓታል።

ከ10 ቀን በፊት በፈጸመው ተመሳሳይ የቦምብ ጥቃት 81 ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.