Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል በሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዝግጅት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣መስከረም 4፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በክልሉ በሚካሄደው 6ኛ ሀገራዊ ምርጫ ለክልል ምክር ቤትና ለፌዴራል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሚወዳደሩ የብልፅግና ፓርቲ እጩዎች ጋር በጅግጅጋ ተወያዩ።

በውይይቱ የሶማሌ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ኢንጂነር መሀመድ ሻሌ እንዲሁም የብልፅግና ፓርቲ እጩዎች ተገኝተዋል።

በመድረኩ በተያዘው ወር በሚካሄደው ምርጫ በፓርቲ ደረጃ የተደረጉ ዝግጅቶች ላይ ውይይት መደረጉን ከሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.