Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች ከ5 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ሚኒስቴር በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የሚውል ከ5 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል፡፡
 
የመስኖና ቆላማ አከባቢ ልማት ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድና የመስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ብርሃኑ ሌንጪሶ ጅግጅጋ ከተማ በመገኘት ለ400 ሶዎች የኢፍጣር መርሐ ግብር አካሂደዋል፡፡
 
በኢፍጣር መርሐ ግብሩ ላይ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድን ጨምሮ የክልሉ መንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
 
ከዚህ በተጨማሪም የመስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ሚኒስቴር በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ አስከፊ ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የሚውል ከ5 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል።
 
ድጋፉን የተረከቡት አቶ ሙስጠፌ “በብዙ የክልሉ አካባቢዎች ዝናብ እየዘነበ ቢሆንም አሁንም ከፍተኛ ድጋፍ የሚሹ ዜጎች ስላሉ፥ ገንዘቡን ለድርቁ ምላሽ ለመስጠት እንጠቀምበታለን” ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.