Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል አይሽአ ላይ የሚገነባው የኢንዱስትሪ ፖርክ ጥናቶችና ቀጣይ ስራዎች ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል አይሽአ ላይ የሚገነባው የኢንዱስትሪ ፖርክ ጥናቶችና ቀጣይ ስራዎች ላይ ውይይት ተካሂዷል።

የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድን ጨምሮ የክልልና የፌደራል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የፌደራል ኢንዱስትሪ ፖርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በአይሽአ ላይ እስከ አሁን ከቦታ መረጣ እስከ የከርሰ ምድር ውሃ ጥናት ውጤቶችን ለተወያዮቹ ያቀረበ ሲሆን ከተወያዮችም የተለያዩ ሐሳቦችና ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

ኮርፖሬሽኑ በቀጣይ በሃያ ዓመታት ረዥም ዕቅዱ በሶማሌ ክልል በጅግጅጋ፣ ጎዴ፣ ቀብሪደሐር፣ ደጋሃቡር፣ ቀላፎና የተመረጡ ቦታዎችን የማልማት ዕቅድ እንዳለው ነው የገለጸው፡፡

ይህም የክልሉን ለልማት ምቹነት የተፈጥሮ ሐብቶችን በመጠቀም ሰፊ የኢንቨስትመንት መዳረሻ እንዲሆን ያስችላል ነው ያለው፡፡

ከዚህ ባለፈም ለዜጎች የሚፈጥረው የስራ ዕድልም ከፍተኛ በመሆኑ በፍጥነት ወደ ስራ መግባት እንዳለበት መገለጹን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.