Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል ውድመት አድርሰዋል የተባሉ 16 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘረፋና ሥርቆት ተሰማርተው በሕዝብና መንግሥት ሀብትና ንብረት ላይ የውድመት አደጋ አድርሰዋል ተባሉ 16 ተጠርጣዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሶማሌ ክልል ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር መሀሙድ ሼክ አህመድ÷ በጅግጅጋ ከተማ በዘረፋና ሥርቆት ተሰማርተው በሕዝብና መንግሥት ንብረት ላይ የውድመት አደጋ አድርሰዋል የተባሉ 16 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ የኢትዮ-ቴሌኮም የቴሌኮሙኒኬሽን መሳሪያዎች፣ የኢትዮጵያ መብራት ኃይል የመስመር ገመዶች እንዲሁም ለጅጅጋ ዩኒቨርሲቲና ጅግጅጋ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት ከሚሰጡት የውሃ ጉድጓዶች አንዱ የሆነውና “ቡሮቆየር” ተብሎ የሚታወቀውን ውሃ ጉድጓድ መሳሪያዎች ለሥርቆትና መበጣጠስ አደጋ የማጋለጥ ወንጀል የተጠረጠሩ መሆናቸው ረዳት ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።
ሕዝቡ በመሰረተ ልማት አውታሮችና አገልግሎቶች ላይ ለአደጋና ሥርቆት የሚያጋልጡ አካላትን እንዲያጋልጥና ከጸጥታ አካላት ጎን እንዲቆም ረዳት ኮሚሽነር መሀሙድ ሼክ አህመድ ጥሪ አቅርበዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.