Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ የምክክር መድረክ አካሄዱ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 17 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሶማሌ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ የምክክር መድረክ በጅግጅጋ ከተማ ተካሄደ።

በዛሬው እለት በጅግጅጋ ከተማ በተካሄደው የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ የምክክር መድረክ ላይ የሶማሌ ክልል ብልፅግና ፓርቲና ሌሎች በክልሉ የሚገኙ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፈዋል።

የምክክር መድረኩ ባለፉት ሰባት ዙሮች ሲካሄዱ የነበሩት የምክክር መድረኮች አካል ሲሆን፥ ለክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ለመጓዝና ለመመራት በተዘጋጀው የስምምነት ሰነድ ላይ ያተኮረ ነው።

ኮንሳይሌሽን ሪሶርስ የተባለው ድርጅት ባዘጋጀው የፖለቲካ ፓርቲዎቹ 8ኛ የምክክር መድረክ ላይ ፓርቲዎቹ አብረው ሊጓዙ በሚችሉባቸው በሰላምና ፀጥታ በምርጫና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ውይይት በማካሄድ በቀጣይ ፓርቲዎቹ የተዘጋጀውን የስምምነት ሰነድ በማጠናቀቅ ለመፈራረም ተስማምተዋል።

ከውይይቱ በኋላ የሶማሌ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ፈይሰል ረሺድ የተዘጋጀው ሰነድ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በመከባበር በህግ አግባብ እንዲንቀሳቀሱ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥርላቸው ነው ብለዋል።

በክልሉ ከለውጡ ጊዜ ጀምሮ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት በተከናወኑ ስራዎች በክልሉ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በነፃነትና በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱበት አውድ መፈጠሩን ሀላፊው ገልፀዋል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉ በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችና በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ተወካዮችም የተዘጋጀው የስምምነት ሰነድ በምርጫና ሌሎች ጉዳዮች በሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት መናገራቸውን የሶማሌ ክልል ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.