Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል የአዋሳኝ ቀጠናዎችን የጸጥታ ሁኔታ ለማጠናከር የመስክ ጉብኝት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20 ፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ከአጎራባች አገራት ጋር ያለውን የአዋሳኝ ቀጠናዎችን የጸጥታ ሁኔታ ለማጠናከር ያቀደ የመስክ ጉብኝት እየተደረገ ይገኛል፡፡
 
በሶማሌ ክልል የጸጥታ ዘርፍ ቢሮ ሀላፊ በአቶ ሙበሽር ዱበድ የሚመራ የጸጥታና የህግ አስፈጻሚ አካላት የተካተቱበት ቡድን ክልሉ ከአጎራባች አገራት ጋር ያለውን የአዋሳኝ ቀጠናዎችን የጸጥታ ሁኔታ ለማጠናከር ያቀደ የመስክ ጉብኝት እያደረጉ መሆኑን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ገልጿል፡፡
 
የሶማሌ ክልል የጸጥታ ዘርፍ ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙበሽር ዱበድ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉ ሲሆን÷ በአሁኑ ወቅት የሶማሌ ክልል በአስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት ውስጥ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
 
የህወሓት የሽብር ቡድን ተላላኪዎች በሶማሌ ክልል ከጎረቤት አገራት ጋር በሚያዋስነው ቀጠና ሰርገው እንዳይገቡ ከሶማሊያ የተለያዩ ግዛቶች፣ ከሶማሊላንድ፣ ከጅቡቲ፣ ከኬንያ የጋራ የድንበር ኮሚሽንና ከጸጥታ ዘርፍ አመራሮች ጋር በጋራ እየሰሩ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
 
የሶማሌ ክልል የልዩ ሀይል ፖሊስ ሰራዊትና የህዝብ ሚሊሻ አደረጃጀት እንዲሁም የማረሚያ ቤቶች የደህንነትና ጸጥታ ዘርፍ ከመከላከያና ከሶማሌ ክልል ማህበረሰብ ጋር በመሆን የክልሉን የአዋሳኝ ቀጠናዎች ሰላምና መረጋጋት ከጸረ- ሰላም ሀይሎች ለመከላከል የሚያስችል ዘርፈ ብዙ ስራ እየተሰራ እንደሆነ የጸጥታ ዘርፍ ሀላፊው ገልጸዋል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለ!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.