Fana: At a Speed of Life!

በሶስት ቋንቋዎች የተሰራ ፊልም ለእይታ ሊቀርብ ነው

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓባይ ወንዝ ዙሪያ የሚያጠነጥን “ሂድ ና” የተሰኘ ፊልም ለእይታ ሊቀርብ ነው::
ፊልሙ በሶስት ቋንቋዎች የተዘጋጀ ሲሆን ከዓባይ መነሻ ሰከላ ጀምሮ የተሰራ አዝናኝና አስተማሪ ፊልም እንደሆነ ተነግሯል::
ፊልሙ የፊታችን ሰኔ 6፣2013 ዓ.ም የሚመረቅ ሲሆን በሀገራችን በዓባይ ላይ ተሰሩ ከሚባሉ ሙዚቃዎችና ፊልሞች በተሻለ አቀራረብ ዓባይ ለኢትዮጵያዊያን ያለውን ፋይዳ የሚያሳይ እንደሆነ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በሚነስቴሩ የባህል ኢንደስትሪ ልማት ዳይሬክተር አቶ ተፈሪ ተክሉ፥ ግብጾች በዓባይ ላይ የሚያተኩሩ ፊልሞች፣ ሙዚቃዎችና የተረትና የመማሪያ መጻህፍትን በማሳተም ዜጎቻቸው ዓባይን እንደ ሕይወታቸው እንዲያዩ በማድረግ ሰፊ ስራ የሰሩትን ያህል በኛ ሀገር ምንም አልተሰራም ብለውዋል፡፡
ይህንንም ከማሻሻል አንጻር ‹‹ሂድ ና›› ፊልም የራሱ ዕሴት ይዞ እንደመጣ ተናግረው፥ ፊልሙ በአማርኛ፣ በእንግሊዝኛ እና በአረብኛ ቋንቋዎች መሰራቱ ደግሞ በዓባይ ላይ የሚከታተሉን የውጩ ዓለም ሰዎች ዓባይ ለኛ ምናችን እንደሆነ እንዲረዱ ያደርጋል ብለዋል፡፡
በፊልሙ ከተወኑ ተዋናዮች መካከል አርቲስት ችሮታው ከልካይ፥ በተቻለን መጠን ታሪክ ሳይዛባ ተጠንቅቀን የሙህራንን አስተያዬት አካተን ከእውነተኛ ቦታው ተገኝተን ነው የሰራነው ፤ ዓባይ ለኢትዮጵያ ሀብቷ፣ ፀጋዋና የመጠቀም መብቷ እንደሆነ በጥበብ ለማሳየት ጥረናል ብሏል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
በሶስት ቋንቋዎች የተሰራ ፊልም ለእይታ ሊቀርብ ነው
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.