Fana: At a Speed of Life!

በሻምፒዮናው ኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹን ወርቅና ብር ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹን ወርቅና ብር ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡

በኮሎምቢያ ካሊ እየተካሄደ ባለው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ሌሊቱን በተደረጉ የ5 ሺህ የወንዶች እና የ3 ሺህ ሜትር የሴቶች የፍፃሜ ውድድሮች ኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹን የወርቅ እና የብር ሜዳሊያዎች አግኝታለች።

በ5 ሺህ ሜትር የወንዶች የፍፃሜ ውድድር አትሌት አዲሱ ይሁኔ በ14 ደቂቃ ከ3 ሰከንድከ5 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት 1ኛ ሆኖ ውድድሩን በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳሊያ አምጥቷል።

በ3 ሺህ ሜትር የሴቶች የፍፃሜ ውድድር ደግሞ አትሌት ፅዮን አበበ በ9 ደቂቃ ከ3 ሰከንድ ከ85 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት 2ኛ ሆና በመግባት የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች።

በወንዶቹ ምድብ አትሌት ገበየሁ በላይ፣ በሴቶቹ ደግሞ አትሌት ብርቱካን ወልዴ 4ኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቅ ዲፕሎማ ማግኘታቸውን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.