Fana: At a Speed of Life!

በሻሸመኔ ከተማ በተደረገ ፍተሻ በርካታ የጦር መሳሪያዎችና ለሽብር የሚውል ቁሳቁስ ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሻሸመኔ ከተማ በአራት ቀበሌዎች በሚገኙ መኖሪያ ቤቶች በተደረገ ፍተሻ በርካታ የጦር መሳሪያዎችና ሌሎች ለሽብር ተግባር የሚውል ቁሳቁስ ተያዘ።

ከጦር መሳሪያና ከቁሳቁስ በተጨማሪም 66 ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የሻሸመኔ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኮሙኒኬሽን ሃላፊ ኢንስፔክተር ታምራት አበበ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ የጦር መሳሪያና ሌሎች ቁሳቁስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ተከትሎ የጸጥታ ሀይሉ በቅንጅት ከህዳር 5 ቀን ጀምሮ በዘመቻ ባደረገው ፍተሻ የተያዙ ናቸው።

በሻሸመኔ ከተማ ቀበሌ 01፣ 03፣ 04 እና 10 በጋራ መኖሪያ ቤትና በግለሰብ ቤቶች ፍተሻዎች ተደርገዋል።

በፍተሻውም 17 የሸኔ አባላትና 59 የጁንታ አባላት በቁጥጥር ስር ሲውሉ 4 ቱርክ ሽጉጥ፣ 3 የእጅ ቦምብ፣ 5 የፌደራል ፖሊስ መለዮ፣ 5 ላፕቶፕ፣ 3 የጦር ሜዳ መነጽር፣ 3 የማረሚያ ቤት ዩኒፎርም፣ 3 የተለያዩ ኮምፒዩተሮች፣ በርካታ ሀሰተኛ መታወቂያና ሌሎች ሰነዶች እንዲሁም ወደ 756 ኪሎ ግራም የሚመዝን ካናቢስ እጽ መያዙን ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈም 161 ባለ ሁለት እግር ሞተር ብስክሌት እና አንድ ግሬደር ፣ አንድ ኤፍ ኤስ አር የጭነት መኪና፣ አንድ ፒ ካፕ እና አንድ ሚኒባስ ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ ውጪ የተለያየ አይነት ድምፅ አልባ መሳሪያዎች፣ የተለያየ አይነት ፎቶ ግራፎችም እንዲሁ ከተጠርጣዎች ዘንድ ተገኝቷል ነው ያሉት።

የከተማዋ ነዋሪ በመደራጀት አከባቢውን ከመጠበቅ ባለፈ መረጃ በመስጠትና በማጋለጥ ላይ እያደረገ ያለው ተሳትፎ የሚበረታታ ነው ብለዋል።

በኃይለኢየሱስ ስዩም

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.