Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የወደሙ የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም ከ11 ቢሊየን ብር በላይ ያስፈልጋል- ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በትምህርት ሚንስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የሚመራ ልዑክ በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ አሸባሪው ህወሓት ወርሯቸው በነበሩ አካባቢዎች ዘረፋና ውድመት የተፈጸመባቸውን ትምህርት ቤቶች ጎብኝቷል፡፡
ልዑኩ በሽብር ቡድኑ ውድመትና ዘረፋ የተፈጸመባቸውን የኮኪት 2ኛ ደረጃ መሰናዶና የደብረዘቢጥ የመጀመሪያ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ት/ቤት ጎብኝቷል፡፡
በጉብኝታውም የትምህርት ቤቶቹ መሰረተ ልማት፣ የመማሪያ ፕላዝማዎች፣ ኮምፒውተሮችና የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁሶች መውደማቸውን ተመልክተዋል፡፡
የሽብር ቡድኑ የተማሪዎችን ወንበሮች ምግብ ለማብሰል ለማገዶነት እንደተጠቀማቸውም በጉብኝቱ ወቅት ተብራርቷል፡፡
በመስክ ጉብኝቱ የትምህርትሚንስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እንደተናገሩት÷ መግደል፣ መዝረፍና ማውደም የአሸባሪው ህወሓት መገለጫ ናቸው ማታውን ከመቄት ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በሽብር ቡድኑ ከፍተኛ የንብረት ዘረፋና ውድመት የተፈጸመባቸውን ት/ቤቶችም መልሶ ለማቋቋም የትምህርት ሚኒስቴር የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡
ትምህርት ቤቶቹን ደረጃቸውን ባሟላ መልኩ እንደገና መልሶ ለማቋቋም የፌዴራልና የክልል መንግስት ከመላው ኢትዮጵያውያን ጋር ተባብረውና ተጋግዘው ትምህርት ቤቶቹን እንደሚገነቡም ተናግረዋል።
በአጠቃላይ በአማራ ክልል የወደሙ የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም ከ11 ቢሊየን ብር በላይ ያስፈልጋል እንደሚያስፈልግም ተመላክቷል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ማተብ ታፈረ ቡድኑ በአማራ ክልል ከአራት ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች ላይ ሙሉ በሙሉና በከፊል ውድመት ማድረሱን ገልጸዋል።
ከትምህርት ሚንስቴር ጋር በመተባበር መልሶ ግንባታዎች በአጭር ጊዜ እንደሚሰራም ቢሮ ሃላፊው መናገራቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.