Fana: At a Speed of Life!

በቀራኒዮ ፀበል አካባቢ በደረሰ ቃጠሎ የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑ 5 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ልዩ ዞን በተለምዶ ቀራኒዮ ፀበል እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በደረሰ የመኖሪያ ቤት ቃጠሎ የአምስት ሰዎች ህይወት አለፈ።
ትናንት ከምሽቱ 5:34 አካባቢ በደረሰው የመኖሪያ ቤት ቃጠሎ አምስት የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
በአደጋው አባትን ጨምሮ ከ4 እስከ 14 ዓመት እድሜ የነበራቸው ህጻናት ናቸው ህይወታቸው ያለፈው።
አደጋውን ለመከላከል 25 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች 3 ከባድ ተሽከርካሪ 2 አምቡላንስ 2 ቀላል ተሽከርካሪ የተሰማሩ ሲሆን÷ በአደጋው 200 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.