Fana: At a Speed of Life!

በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በአፋር ክልል የተገነባው13ኛው ትምህርት ቤት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በአፋር ክልል አውሲ-ረሱ ዞን ዱብቲ ወረዳ የተገነባው13ኛው የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ ተመረቀ።

በጽህፈት ቤቱ ከተገነቡት 20  ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ የሆነዉ ዱብቲ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው ዛሬ ተመርቋል።

በአፋር ክልል የተመረቀው በምረቃው ስነ ስርአት ላይ ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያችውን ጨምሮ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ፣የሀገር ሽማግሌዎች፣ ሌሎች የስራ ሃላፊዎች  እንዲሁም ተማሪዎች ተገኝተዋል::

ትምህርት ቤቱ በ13 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ወጪ የተገባ ነው።

ትምህርት ቤቱ በውስጡ  የአስተዳደር ህንጻ፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ ሙከራ፣ ቤተ መጽሐፍት፣ የስብሰባ አዳራሽ እና የመጸዳጃ ህንጻዎችን አካቷል፡፡

ትምህርት ቤቱ በሙሉ አቅሙ መቀበል ሲጀምር በሁለት ፈረቃ 1 ሺህ 800 ተማሪዎችን የመቀበል አቅም እንዳለው ተነግሯል፡፡

በትምህርት ቤት ርቀትና እጥረት ምክንያት ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ገበታ ላልላኩ የዱብቲ ወረዳና  እንዲሁም አዋሳኝ ቀበሌ ነዋሪዎች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት በመላክ እድሉን እንዲጠቀሙ ጽህፈት ቤቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ጽህፈት ቤቱ በዛሬው እለት ያስመረቃችውን ጨምሮ እንደ ሃገር ግንባታችው ተጠናቆ ያስመረቃቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 13 የደረሱ ሲሆን ቀሪዎቹን በቅርብ ቀን እንደሚያስመርቅ ተገልጿል፡፡

በፍሬህይወት ሰፊው

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.