Fana: At a Speed of Life!

በቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት በሲዳማ ክልል የተገነባው ትምህርት ቤት ተጠናቆ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት በሲዳማ ክልል ሀኮ ወረዳ የተገነባው 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተጠናቆ ተመርቋል፡፡
ትምህርት ቤቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በተገኙበት ነው የተመረቀው።
ትምህርት ቤቱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የመጽሐፍ ሽያጭ በተገኘው ገቢ በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት የተገነባ ሲሆን፥ ለግንባታውም 11 ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጎበታል።
ትምህርት ቤቱ 12 የመማሪያ ክፍሎችን ጨምሮ ሁለት ቤተ ሙከራ እና አንድ ቤተመጻሕፍት አለው።
በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዳይሬክተር ኢንጂነር ሃብታሙን ጨምሮ የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት በሲዳማ ክልል የመጀመሪያውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው ያስመረቀው።
ፅህፈት ቤቱ በሁለተኛው ዙር ካስገነባቸው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ይህ ሶስተኛው ሲሆን በጥቅሉ 23 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን አስመርቋል።
በሃይማኖት ኢያሱና ታሪኩ ለገሰ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.