Fana: At a Speed of Life!

በቀጣይ አመት በኦሮሚያ ክልል 300 መቶ ሺህ ሄክታር መሬት በስንዴ እንደሚለማ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 24 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቀጣይ አመት በኦሮሚያ ክልል 300 መቶ ሺህ ሄክታር የሚሆን መሬት በስንዴ እንደሚለማ የኦሮሚያ ግብርና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

በዚህም ከሚለማው መሬት 26 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት እንደታቀደ የክልሉ ግብርና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ዳባ ደበሌ ገልጸዋል።

ቢሮው የ2012 ዓ.ም የስራ አፈፃፀም እና በቀጣይ 2013 ዓ.ም የስራ እቅድ ላይ በአዳማ ከተማ ውይይት አካሂዷል።

በዚህም በ2012 ዓ.ም ከተሰሩ ስራዎች መካከል ከዝናብ ጥገኝነት በመውጣት በመስኖ ማልማት ወደ ሜካናይዜሽን መሻገር ፣ በክላስተር በማምረት 600 ፐርሰንት 10 ሚሊየን ኩንታል ጭማሪ ማሳየቱ በጥሩ ጎን መታየቱን የቢሮው ሃላፊ አቶ ዳባ ደበሌ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የተሰሩ ስራዎች በሁሉም ቦታ በእኩል ለማዳረስ እና የበቆሎ ምርጥ ዘርን በበቂ ሁኔታ ለአርሶ አደሩ ለማዳረስ አለማቻሉን እንደክፍተት መታየቱንም ሃላፊው አንስተዋል።

በቀጣይ በ2013 ዓ.ም ሌሎች የግብርና ስራዎችን በመስራት በልዩነት ከውጪ የሚገባውን ስንዴ ለማስቀረት በትኩረት እንደሚሰራ ተጠቅሷል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት ኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ÷ ህዝብ እና አገር እጃችንን እየጠበቁ ነው ብለዋል።

ዜጎች ከድህነት በመውጣት በምግብ እራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ ሁላችንም የሚጠበቅብንን ግዴታ በአግባቡ መወጣት አለብን ለዚህም የክልልሉ መንግስትም የሚጠበቅበትን ድጋፍ ያደርጋል ነው ያሉት ።

በዳግማዊ ዴክሲሳ

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.