Fana: At a Speed of Life!

በቀጣይ ዓመት በ255 ሚሊየን ብር የ22 የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናትና ዝርዝር ዲዛይን ስራዎች እንደሚከናወኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 19 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ጥቅም ላይ መዋል የሚችሉ 22 መካከለኛና ትላልቅ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶችን የአዋጭነት ጥናትና ዝርዝር ዲዛይን ስራዎች እንዲሁም ክለሳ በ2013 በጀት ዓመት በማከናወን ለግንባታ ምቹ የማድረግ ስራዎች እንደሚከናወኑ ተገለፀ።

የሁሉም ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናትና ዝርዝር ዲዛይን ማከናወኛ 255 ሚሊየን ብር በጀት መያዙ ተነግሯል።

በበጀት ዓመቱ የሚጀመሩት 8 የመስኖ ልማት የአዋጭነት ጥናትና ዝርዝር ዲዛይን ፕሮጀክቶች በአማራ ክልል 2 ፣በደቡብ ክልል 2 ፣ በኦሮሚያ ክልል 3 እንዲሁም በሱማሌ ክልል 1 ናቸው።

ፕሮጀክቶቹም የሽንፋ ፣የአንገረብ ፣የወይጦ፣የሽፌ፣የሞርሞራ ፣የታችኛው ገናሌ ፣የወይብ እና የቡልደሆ መሆናቸውን የመስኖ ልማት ኮሚሽን አስታውቋል።

በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ 7 ፕሮጀክቶች የጥናትና ዲዛይን ስራቸው ተከልሶ ወደ ግንባታ እንዲገቡ ታቅዶ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

እነዚህ ፕሮጀክቶችም መገጭ ፣ግልገል አባይ ፣ጀማ ፣ብላቴ ፣ ዳቡስ ፣ ጎሎልቻ እና ገላና ግድብና መስኖ መሰረተ ልማት ሲሆኑ የጥናትና ዲዛይን ክለሳ ስራዎች እስከ ህዳር ወር ድረስ ለማጠናቀቅ ታቅዷል፡፡

በ2012 በጀት ዓመት 7 የአዋጭነት ጥናትና ዝርዝር ዲዛይን የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶችን በ6 ክልሎች ማለትም በትግራይ፣ በአማራ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ እና በደቡብ ክልሎች አንዳንድ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ሁለት የተከናወኑ ሲሆን በ2013 በጀት ዓመት ሁሉም ይጠናቀቃሉ ተብሎ ይጠበቃል ፡፡

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.