Fana: At a Speed of Life!

በቀጣዮቹ 10 ቀናት በሃገር አቀፍ ደረጃ ከ25 ሚሊየን በላይ ሰዎችን የኮቪድ-19 ክትባት ለመከተብ ታቅዷል

አዲስ አበባ፣ሰኔ 4፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በድሬዳዋ አስተዳደር ሶስተኛው ዙር የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት በይፋ መሰጠት ተጀምሯል፡፡

በአስተዳደሩ የሦስተኛው ዙር የኮሺድ 19 መከላከያ ክትባት የኢፌዲሪ ጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ በተገኙበት በይፋ መስጠት ጀምሯል።

በሃገር አቀፍ ደረጃ በ25 ሚሊየን በላይ ሰዎችን በቀጣዮቹ 10 ቀናት ለመከተብ ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን ዶክተር ደረጀ አስታወቀዋል።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከጤና ስጋትንነቱ ባሻገር በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ የመከላከያ ክትባትን መውሰድ አማራጭ የሌለው የመከላከያ ዘዴ በመሆኑ ለዘመቻው ስኬታማነት ሁሉም አስተዋፅዖውን እንዲያበረክት ጠይቀዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር በበኩላቸው በአስተዳደሩ ከዚህ በፊት በተሰጡት የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ውጤታማ እንዲሆን የሃይማኖት ተቋማትና አባቶች ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አመሰግነው፥ ሁሉም ህብረተሰብ ክትባቱን እንዲወስድ የመንግስት ተቋማትና ሌሎችም ድጋፍ እንዲያደርጉ አሳሰበዋል።

በድሬዳዋ አስተዳደር በቀጣዮቹ አስር ቀናት በሁሉም የመንግስት የጤና ተቋማትና በተመረጡና በጊዜያዊነት በሚቋቋሙ የክትባት መስጫ ጣቢያዎች ክትባቱ እንደሚሰጥ ተገልጿል::

 

በተሾመ ኃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.