Fana: At a Speed of Life!

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በተሽከርካሪ ላይ በተደረገ ፍተሻ የተለያዩ ሽጉጦች እና ጥይቶች  ተያዙ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 30 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በተሽከርካሪ ላይ በተደረገ ፍተሻ የተለያዩ ሽጉጦች እና ጥይቶች  እንደተያዙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ጥቃት ለመፈፀም እና ሰላም ለማደፍረስ በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ የሚያደርገውን ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2A-41649 አ.አ የሆነ ተሽከርካሪ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ  አራት በተለምዶ 31 ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲደርስ ነበር ለፍተሻ እንዲቆም በፖሊስ አባላት የተጠየቀው፡፡

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ስለሺ ሸንቁጤ እንደገለፁት÷ በተሽከርካሪው ውስጥ በተደረገ ፍተሻ 4 የተለያዩ ሽጉጦች፣30 የክላሽ ጥይቶች ከነካርታው እና 39 የሽጉጥ ጥይቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በዚህ ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ላይ የተሳተፉ ሶስት ተጠርጣሪዎች ከእነተሽከርካሪው ተይዘው ምርመራ እየተደረገ  እንደሚገኝም ምክትል ኢንስፔክተር ስለሺ አስረድተዋል፡፡

ከህወሓት በተሰጣቸው የጥፋት ተልዕኮ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች ጥቃት ለመፈፀም እና ሰላም ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ አካላት ዕቅዳቸው እንዳይሳካ ለማድረግ ከህብረተሰቡ እና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር  ተባብሮ እየሰራ መሆኑንና አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.