Fana: At a Speed of Life!

በበርሃሌ ግንባር የህወሓት ሽብር ቡድን አባላት እና የጦር መሳሪያዎች ተማረኩ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል በርሃሌ ግንባር ትናንት በነበረ ውጊያ የህወሓትሽብር ቡድን አባላት እና በርካታ የጦር መሳሪያዎች ተማርከዋል፡፡
ከተማረኩ የጦር መሳሪያዎች መካከልም ብሬን፣ ክላሽንኮቭ፣ የጦር ሜዳ መነጸር እና በርካታ ቁጥር ያላቸው ተተኳሸ ጥይቶች ይገኙበታል፡፡
 
 
የበርሃሌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ኢብራሂም ኡስማን ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ÷ነዋሪዎችአጎራባች ከሆነው የትግራይ ህዝብ ጋር መልካም ግንኙነት እንደነበራቸው አንስተዋል፡፡
 
 
ይሁን እንጂ አሸባሪው የህወሓትቡድን በወረዳው አርሶ አደሮች ላይ በፈጸመው ጥቃት በርካት ንጹሃን ዜጎችን ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸውን ተናግረዋል፡፡
 
የሽብር ቡድኑ ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ በርሃሌን ተቆጣጥረናል የሚል የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ቢነዛም በአካባቢው የአፋር ህዝብና ልዩ ሃይል በጋራ በወሰዱት የመልስ ምት የጁንታው ሃይል እየተደመሰሰ ነው ብለዋል፡፡
 
በትናንትናው ዕለት እና ከትናንት በስቲያ በነበረው ውጊያም የጁንታው ሃይል በርካታ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል ነው ያሉት፡፡
በአካባቢው ሰርጎ በመግባት ኢትዮጵያን ለማፍረስ እቅድ የያዘው የህወሓት ሽብር ቡድን የአፋር ህዝብ እያለ መቼም እንደማይሳካለት ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
ህወሓት የመላው ኢትዮጵያ ጠላት ነው ያሉ ነዋሪዎቹ ÷ የሽብር ቡድኑ በሙሉ እስኪደመሰስ ድረስ ከጸጥታ ሃይሉ ጋር በቅንጅት እንደሚታገሉት አንስተዋል፡፡
 
 
በጌታሰው የሺዋስ እና ታሪኩ ለገሰ
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.