Fana: At a Speed of Life!

በበጀት አመቱ ስድስት ወራት ከወጪ ንግድ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በበጀት አመቱ ግማሽ አመት ከወጪ ንግድ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን አስታወቀ፡፡

በስድስት ወራት ውስጥ 1 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር ከወጪ ንግድ ለማግኘት ታቅዶ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገልፀዋል፡፡

በግማሽ ዓመቱ ቀልጣፋ፣ ዘመናዊና ተደራሽ የንግድ አሰራር ለማስፈንና የወጪ ንግዱን ለማሳደግ በትኩረት መሰራቱንም ተናግረዋል፡፡

ይህም ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር ጋር ሲነፃፀር የ18 በመቶ ብልጫ አሳይቷል ነው ያሉት።

ቡና፣ አበባ፣ ጫት፣ የቅባት እህሎችና ጥራጥሬ እንዲሁም ማዕድናት ወደ ውጪ ከተላኩ ምርቶች ዋና ዋናዎቹ ናቸው መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.