Fana: At a Speed of Life!

በበጀት ዓመቱ ለሚከናወኑ የስነ ምድር ሀብት ጥናት የቅድመ ቅኝት ስራ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ በበጀት ዓመቱ ለሚከናወኑ የስነ ምድር ሀብት ጥናት የቅድመ ቅኝት ስራ አጠናቀቀ፡፡
በአምስት ቡድን የተከፈለው የቅኝት ቡድን ከጥቅምት 20 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የስነ-ምድር ጥናት በሚከናወንባቸው የአማራ፣ የኦሮሚያ፣ የደቡብ፣ የሶማሌ እና የአፋር ክልሎች ላይ ሲያካሂድ የቆየውን የቅድመ የቅኝት ስራ አጠናቋል፡፡
ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፉ ልታገኝ የሚገባውን የውጭ ምንዛሬ ለማሳደግና የዜጐችን ስራ አጥነት ለመቀነስ በሚያስችል መልኩም በተያዘው በጀት ዓመት በእነዚህ ክልሎች ጥናት ለማድረግ ሰርቬዩ እቅድ ይዞ እየሰራ እንደሚገኝም ገልጿል፡፡
ከዚህ በፊት በአንዳንድ ክልሎች ለስነ-ምድር ጥናት በሚወጡ የሰርቬዩ የስነ ምድር ሃብት ጥናት ባለሙያዎች ላይ እንግልትና ስቃይ ይደርስ እንደነበር የሚናገሩት የቅኝቱ ተሳታፊዎች ይህን ለማስቀረት ከክልል የማዕድን ቢሮዎች ጋር በቅንጅት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
ሰርቬዩ በበጀት ዓመቱ ለሚከናወኑ የስነ ምድር ሀብት ጥናት የቅድመ ቅኝት ስራ በማከናወን ከክልል እና ከዞን የማዕድን ቢሮዎች ጋር በቅንጅት ለመስራት የስምምነት ሰነድ መፈራረሙን ከኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.