Fana: At a Speed of Life!

በቡሩንዲ ዋና ከተማ በመሬት መንሸራተት አደጋ የ15 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 14፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቡሩንዲ ዋና ከተማ ቡጅምብራ በመሬት መንሸራተት አደጋ ቢያንስ የ15 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ።

ቅዳሜና እሁድ የነበረው ከባድ ዝናብ ያስከተለው የመሬት መንሸራተት ቢያንስ የ15 ሰዎች ህይወት ሲቀጥፍ 30 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የቡጅምብራ ከንቲባ ገልፀዋል።

በዚህ አደጋ የብዙ ሰዎች መኖሪያ ቤት መውደሙም ተገልጿል።

አንጌላ የተባለች የ50 ዓመት እናት መኖሪያ ቤቷ መውደሙን ተከትሎ አራት ልጆቿን እና ባለቤቷን ማጣቷን ተናግራለች።

የሀገሪቱ የጸጥታ ሚኒስትር አሊየን ጉኢላኡሜ በአደጋው የተጎዱ አካባቢዎችን የጎበኙ ሲሆን፥ በአደጋው መኖሪያ ቤታቸው የወደመባቸው ዜጎች ጊዚያዊ መጠለያ ይቀርብላቸዋል ብለዋል።

በቅርብ ሳምንታት ውስጥ በምሥራቅ አፍሪካ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነግሯል።

የቡሩንዲ ባለሥልጣናት በበኩላቸው በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ቢያንስ 28 ሰዎች በመሬት መንሸራተት እንደሞቱ ነው የገለፁት።

 

ምንጭ፦ ሲ.ጂ.ቲ.ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.