Fana: At a Speed of Life!

በቡራዩ በደረሰ የእሳት አደጋ ግምቱ 10 ሚሊየን ብር የሆነ ንብረት መውደሙ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቡራዩ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ ግምቱ 10 ሚሊየን ብር የሆነ ንብረት መውደሙ ተገለፀ፡፡

ትናንት ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ በደረሰው የእሳት አደጋ ግምቱ 10 ሚሊየን ብር የሆነ ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

አደጋው የደረሰው በቡራዩ ከተማ ገፈርሳ ኖኖ ቀበሌ ልዩ ስሙ ገብርኤል በሚባል አካባቢ ሲሆን በ16 ሱቆች፣ በ3 መኖሪያ ቤቶችና 3 ባርና ሬስቶራንቶች ላይ ቃጠሎ ደርሷል።

የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በአደጋው 10 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።

“እሳቱ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያስከትል በመቆጣጠር 25 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን ተችሏል” ብለዋል።

በአደጋው በሰው ላይ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰ ጠቁመው፤ እሳቱን ለመቆጣጠር ከአንድ ሰዓት ተኩል በላይ ጊዜ መውሰዱን ተናግረዋል።

እሳቱን በማጥፋት የኮሚሽኑ ሰራተኞች፣ የፌደራልና የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ አካላትና የአካባቢው ነዋሪዎች መሳተፋቸውንም ገልጸዋል።

የአደጋው መንስዔ ገና እየተጣራ ሲሆን ህብረተሰቡ ለእሳት አደጋ መንስዔ ከሆኑ ተቀጣጣይ ነገሮች እንዲጠነቀቅ አሳስበዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.