Fana: At a Speed of Life!

በቡራዩ በፀጥታ ሃላፊና ሌሎች ሰዎች ላይ ጥቃት በማድረስ ህይወት ያጠፉ አካላትን ተከታትሎ እርምጃ እንደሚወስድ ፖሊስ ገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቡራዩ ከተማ አስተዳደርና ጸጥታ ክፍል ሃላፊ እንዲሁም በሌሎች ሰዎች ላይ ጥቃት በማድረስ ህይወት ያጠፉ አካላትን ተከታትሎ እርምጃ እንደሚወስድ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።

ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ የቡራዩ ከተማ የአስተዳደርና ጸጥታ ክፍል ሃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ ትናንት በተፈፀመባቸው ጥቃት ህይወታቸው ማለፉን አስታውቋል።

ሌሎች ሶስት ሰዎችም ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ ይገኛሉ ነው ያለው።

ከዚህ ጥቃት ጋር በተያያዘ ፖሊስ የምርመራ ስራ መጀመሩንም ነው ኮሚሽኑ በመግለጫው ያስታወቀው።

የህግ የበላይነትን ለማስከበርና ወንጀለኞችን አድኖ በመያዝ ለፍርድ ለማቅረብ ቀን ከለሊት እንደሚሰራም አረጋግጧል።

ኮሚሽኑ ህዝቡ ደህንነቱ እንዲረጋገጥ ከመንግስት አካላት ጋር በንቃት አብሮ እንዲሰራ ጥሪ አቅርቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.