Fana: At a Speed of Life!

በቢሻን ጉራቻ ከተማ አስተዳደር የምርጫ ሂደቱ በሰላም እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቢሻን ጉራቻ ከተማ አስተዳደር የምርጫ ሂደቱ በሰላም እየተካሄደ መሆኑ ተገለፀ፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ቅኝት እንዳደረገው አራት የምርጫ ጣቢያዎች ባሉባት ቢሻን ጉራቻ የምርጫ ክልል ማህበረሰቡ በጠዋት ወጥቶ ድምፅ መስጠት ጀምሯል።

በቢሻን ጉራቻ ምርጫ ጣቢያ ሀ የሶስት ፖርቲ ተወካዮች ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚወዳደሩ ሲሆን ለኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት በሶስት ፓርቲ የተወከሉ ሰባት እጩዎች እየተወዳደሩ ይገኛሉ።

በምርጫ ጣቢያው አስተባባሪ አቶ ቃሲም ቱሜ ምርጫው ያለምንም ችግር እየተካሄደ ነው ብለዋል።

ነዋሪዎችም የምንፈልገውን ፓርቲ መርጠናል ፤የሚመጣውንም ውጤት በፀጋ እንቀበላለን ብለዋል።

በምስክር ስናፍቅና ጥላሁን ይልማ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.