Fana: At a Speed of Life!

በቢሾፍቱ ከተማ በጥይት የአንድን ግለሰብ ህይወት ያጠፋውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ለማዋል ምርመራ ተጀምሯል – ፖሊስ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቢሾፍቱ ከተማ በጥይት ተኩሶ የአንድን ግለሰብ ህይወት ያጠፋውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ለማዋል ምርመራ መጀመሩን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዠ ኮማንደር ታሪኩ ለገሰ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ ፣ በትናንትናው ዕለት በግምት ከምሽቱ 3፡00 ላይ መምህር ግርማ ሞገስ የተባሉ ግለሰብን ለጊዜው ማንነቱ ያልታወቀ ተጠርጣሪ በጥይት ተኩሶ መግደሉን ተናግረዋል፡፡

ድርጊቱ የተፈጸመውም ሟች መምህር ግርማ ከአዲስ አበባ ሰርግ ውለው መኪናቸውን ጎረቤታቸው ቤት ግቢ ውስጥ ለማሳደር እያስገቡ ባሉበት ወቅት ነው ብለዋል።

የተኩስ ድምጽ ሲሰማ ፖሊስ በፍጥነት በአካባቢው መድረሱን የተናገሩት ኮማንድር ታሪኩ፥ የመምህር ግርማን ህይወት ለማትረፍ ወደ ሆስፒታል ቢወሰዱም ህይታቸው ማለፉን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በፊት ከመምህር ግርማ ጋር ግጭት የነበራቸው ግለሰቦች ያስፈራሯቸውእና ይዝቱባቸውእንደነበር መረጃ መገኘቱን በመጥቀስም፥ ከእነዚህ ግለሰቦች ውስጥ አንዱ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ከግድያው ጋር ተያይዞ ህይወታቸው ያለፈው ግለሰብ የፖለቲካ ፓርቲ አባል ናቸው የሚለውን ለማረጋገጥ እየተጣራ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ጥቃቱን የፈጸመውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ለማዋል የከተማው ፖሊስ ከኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ጋር በ በመቀናጀት የምርመራ ቡድን ተቋቁሞ ክትትል እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.