Fana: At a Speed of Life!

በባህር ዳር ከተማ ለ1 ሺህ አቅመ ደካማ ወገኖች ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ክልል በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ለ1 ሺህ አቅመ ደካማ ወገኖች ድጋፍ አደረገ፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ለእያንዳንዳቸው 50 ኪሎ ግራም ዱቄት እና 5 ሊትር ዘይት ድጋፍ መደረጉን አስታውቀዋል።

ድጋፉ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል የተጀመረውን የመረዳዳት ባህል ለማጠናከር ያለመ መሆኑንም ነው ያስታወቁት።

ርዕሰ መስተዳድሩ መጭውን የክረምት ጊዜ በመደጋገፍና በመረዳዳት ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች በማካፈል ማሳለፍ ይገባል ሲሉም ህብረተሰቡ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ድጋፉ በሌሎች ከተሞች እንደሚቀጥልም ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.