Fana: At a Speed of Life!

በባህር ዳር ከተማ በ800 ሚሊየን ብር ወጪ እየተገነባ የሚገኘው የብረታብረት ፋብሪካ ማምረት ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህር ዳር ከተማ በ800 ሚሊየን ብር እየተገነባ የሚገኘው “ራቫል ስቲል ማኑፋክቸሪንግ” ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ የብረታብረት ፋብሪካ ማምረት ጀመረ፡፡
በአራት የግንባታ ምዕራፎች ተከፍሎ እየተገነባ የሚገኘው ፋብሪካው ለግንባታ ግብዓት የሚሆን ፌሮ ብረት ማምረት የሚስችለውን የመጀመሪያውን የብረት ምርትና ለህክምና የሚያገለግል ኦክስጅን ማምረት መጀመሩን የፋብሪካው የሰው ኃብት መምሪያ ስራ አስኪያጅ አቶ መንግስቱ አርቄ ተናግረዋል፡፡
አሁን ላይ በሦስት ፈረቃ የሚሰሩ ከ500 በላይ ሰራተኞች እንዳሉት የገለጹት አቶ መንግስቱ የፋብሪካው ግንባታ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ 10ሺህ ቋሚና ጊዜያዊ ሰራተኞችን የስራ ዕድል ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ስራ አስኪያጁ አክለውም ፋብሪካው ሁለተኛ የግንባታ ምዕራፍ ላይ በመሆኑ በ2014 ዓ/ም መስከረም ወር ላይ ፌሮ ብረት ማምረት እንደሚጀምርና ለሐገር ውስጥ ገበያ እንደሚያቀርብ መግለፃቻን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የፋብሪካው ባለቤትና ስራ አስኪጅ ሻም ራቭል በበኩላቸው ፋብሪካው ከ3 ዓመት በፊት በክልሉ የኢንቨስትመንት ፈቃድ አግኝተው ግንባታ በመጀመራቸው እና በመንግስት በኩል እየተደረገላቸውን ስላለው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.