Fana: At a Speed of Life!

በባህር ዳር ዳያስፖራው የሚሰማራባቸው ልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ተዘጋጅተዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዳያስፖራው የሚሰማራባቸው ልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች መዘጋጀታቸውን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ገለጸ፡፡
 
ከልዩ ልዩ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ የዳያስፖራ አባላት በባሕር ዳር ከተማ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች እና የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎችን ጎብኝተዋል።
 
የጉብኝቱ ዓላማ የዳያስፖራ አባላቱ በዘርፉ ሙሉ ግንዛቤ ኖሯቸው በከተማዋ የኢኮኖሚ መነቃቃት እንዲፈጥሩ ማስቻል መሆኑ ተገልጿል፡፡
 
በተለይ የኢንቨስትመንት አማራጮችን አይተው መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈስሱ ፍላጎት መኖሩን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኀላፊ ብርሃን ንጉሤ ተናግረዋል፡፡
 
እንደ ክልል በኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ዘርፉ በርካታ ውድመት መድረሱን ያነሱት መምሪያ ኀላፊዋ ÷ዘርፉ ከደረሰበት ኪሳራ እንዲያንሰራራ መሥራት ይገባል ነው ያሉት፡፡
 
ለዚህም ዳያስፖራው በከተማ አስተዳደሩ የሚሰማራባቸው ልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች መዘጋጀታቸውን ነው የተናገሩት፡፡
 
ለዚህም ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጠር በመግለጽ÷ዳያስፖራዎች ሀብትና እውቀታቸውን ፈሰስ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
 
በመርሃ ግብሩ የተሳተፉ የዳያስፖራ አባላት በበኩላቸው ÷በውጪ አገራት ለረጅም ጊዜ ያጠራቀሙትን ሃብት ጥቅም ላይ እንዲያውሉ የሚያነሳሳ ጉብኝት ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል፡፡
 
መንግሥትም አጋጣሚውን ሊጠቀምበት እንደሚገባ መጠቆማቸውን አሚኮ በዘገባው አስፍሯል፡፡
 
ዳያስፖራው ከመንግሥት ጋር በመቀናጀት ትልቅ ልማት መሥራት ይችላል ያሉት አባላቱ÷ለዚህም ያለውን ጸጋ በአግባቡ መጠቀም እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.