Fana: At a Speed of Life!

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በተደረገ ጨዋታ ባሕር ዳር ከተማ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በተደረገ ጨዋታ ባሕር ዳር ከተማ አዳማ ከተማን 1 ለ 0 አሸነፈ፡፡
የጣናው ሞገድ ማሸነፉን ተከትሎ በ 29 ነጥብ ደረጃውን አሻስሎ 10ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ÷ ቡድኑ በተከታታይ ነጥብ መጣሉን ተከትሎ ትችት ውስጥ ለነበሩት አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የዛሬው ድል እፎይታን ፈጥሯል፡፡
በአንጻሩ አዳማ ከተማ የዛሬውን ሽንፈት ተከትሎ ደረጃውን ለጣናው ሞገድ አስረክቦ÷ አርባ ምንጭ እና ድሬ ዳዋ ከተማን በግብ ክፍያ በመበለጥ 11 ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
ረፋድ ላይ አዲስ አበባ ከተማ ከድሬ ዳዋ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ በአቻ ውጤት መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡
የ24ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሲቀጥል አርባ ምንጭ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ ምሽት 10 ሰዓት ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.