Fana: At a Speed of Life!

በብሄር ሳንለያይ የአከባቢያችንን ሰላም እንጠብቃለን- የማንዱራ ወረዳ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በብሔር ሳንለያይ የአካባቢያችንን ሰላም እንጠብቃለን ሲሉ በመተከል ዞን የማንዱራ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ።

የመተከል ዞን  የተቀናጀ ግብረ ሃይል ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ ከማንዱራ ወረዳ ነዋሪዎች ጋር በወረዳው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

ሌተናል ጄኔራል አስራት በዚህ ወቅት እንደተናገሩት በወረዳው ባሉ ሁሉም ቀበሌዎች ከህዝብ ጋር በመቀናጀት በተሰራ ስራ አንፃራዊ ሰላም ማረጋገጥ ተችሏል።

የታየው ሰላም የአካባቢው ነዋሪዎች አንድነታቸውን አስጠብቀው በሰሩት ውጤታማ ስራ ነው ብለዋል።

“የእኛ ህዝብ እርስ በእርሱ የተጋባ፣ የተዋለደ እና በማህበራዊ ህይወት የተሳሰረ ስለሆነ ሰላም እና አንድነትን አስጠብቆ በአካባቢው ያለውን የተፈጥሮ ሃብት ተጠቅሞ መልማት ይቻላል” ሲሉ ተናግረዋል።

የአካባቢውን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ ከሁሉም ማህበረሰቦች የተውጣጡ ሚልሻዎች ተመልምለው ሥልጠና እየተሰጣቸው እንደሆነም አስታውቀዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው የማንዱራ ነዋሪዎች እርስ እርስ የተጋቡ፣ የተዋለዱ እና በማህበራዊ ህይወት የተሳሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአካባቢያችን እየታየ ያለው የጸጥታ ችግር የፀረ ሰላም ሃይሎች የፈጠሩት እንጂ የማህበረሰቡ አይደለም ብለዋል።

ይህን ችግር በአጭር ጊዜ ማጥፋት የሚቻለው በቅንጅት ስሰራ መሆኑን ገልጸው “ሰላም ለሁሉም ማህበረሰብ መስፈን አለበት” ብለዋል።

ከሁሉም ማህበረሰብ ከተመለመሉት ሚልሻዎች ጋር ተባብሮ በመስራት አካባቢያቸውን ከፀረ ሰላም ሃይሎች እንደሚጠብቁም  መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በመተከል ዞን የተቋቋመው የተቀናጀ ግብረ ሃይል በዞኑ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.