Fana: At a Speed of Life!

በብሪታንያ ጠቅላላ ምርጫ የጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ወግ አጥባቂ ፓርቲ አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በብሪታንያ ጠቅላላ ምርጫ የጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ወግ አጥባቂ ፓርቲ ማሸነፉ ተነገረ።

ትናንት በተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ገዥው ፓርቲ ከ360 በላይ መቀመጫዎችን በማግኘት በሰፊ የድምጽ ልዩነት ማሸነፉን ይፋ የሆኑ የምርጫ ውጤቶች አመላክተዋል።

ፓርቲው ምርጫውን ማሸነፉን ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ብሪታንያ ከህብረቱ ጋር የምትፈጽመውን ፍቺ በቀጣዩ ወር ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

የቦሪስ ጆንሰን ዋነኛ ተፎካካሪ የሆነው ሌበር ፓርቲ ከፈረንጆቹ 1935 ወዲህ ዝቅተኛ የተባለውን ድምጽ ማግኘቱ ተነግሯል።

ሌበር ፓርቲ በጠቅላላ ምርጫው 203 ድምጽ ማግኘቱ ነው የተነገረው።

ከምርጫው ውጤት ይፋ መሆን በኋላ ቦሪስ ጆንሰን የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

የምርጫ ውጤቱ ቦሪስ ጆንሰን ሃገራቸውን ከህብረቱ ማስወጣት የሚችሉበትን ይሁንታ ስለማግኘታቸው አመላካች ነውም ተብሏል።

በብሪታንያ በታህሳስ ወር ምርጫ ሲካሄድ ከ100 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ እና ሬውተርስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.