Fana: At a Speed of Life!

በብራዚል በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ዜጎች ቁጥር ከ 600 ሺህ ማለፉ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በብራዚል በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ዜጎች ቁጥር ከ 600 ሺህ ማለፉ ተገለፀ፡፡
በዚህም ብራዚል ከአሜሪካ ቀጥሎ ከፍተኛ የሞት ቁጥር ያስመዘገበች ሁለተኛዋ ሀገር ሆናለች፡፡
እየጨመረ በመጣዉ የዜጎች ሞት የብራዚሉ ፐሬዚደንት ጄር ቦለሶናሮ ከፍተኛ ትችት እየደረሰባቸዉ መሆኑ ነዉ የተገለፀዉ፡፡
በቫይረሱ ተይዘዉ የነበሩት ፕሬዚደንቱ የቫይረሱን ገዳይነት በማቃለላቸዉና የሃገሪቱ ዜጎች የቫይረሱን ክትባቱን እንዲወስዱ ግፊት ባለማድረጋቸዉ በሃገሪቱ የጤና ባለሙያዎች ተቃዉሞ ገጥሟቸዋል::
ፕሬዚደንቱ ባለፉት በርካታ ወራት ውስጥ የተቃውሞ ሰልፎች ገጥሟቸዉ የነበረ ሲሆን፣ ሰልፈኞች የብራዚል መንግስትን የኮቪድ 19 ፖሊሲዎች በመቃወም እገዳዎች እንዲነሱም ነው የጠየቁት፡፡
የብራዚል ሴኔት በሚያዝያ ወር በወረርሽኙ ዙሪያ የተቀመጡ ፖሊሲዎች ላይ ምርመራ በማድረግ አሻሽሏል።
70 በመቶ የሚሆኑት የሀገሪቱ ዜጎች የመጀመሪያ ዙር ክትባት መዉሰዳቸዉ ቢገለፅም÷ የሟቾች ቁጥር ግን እየጨመረ መሆን ነዉ አልጄዚራ የዘገበው፡፡
በሚኪያስ አየለ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.