Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ አካባቢዎች ለመከላከያ ሠራዊት የሚደረገው ድጋፍ እንደቀጠለ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ለመከላከያ ሠራዊት የሚደረገው ድጋፍ እንደቀጠለ ነው፡፡
የኦሮሚያ ክልል ለመከላከያ ፣ለልዩ ኃይልና ሚሊሻ 650 ሰንጋዎችን ፣ 680 በግና ፍየሎችን ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፍን የክልሉ ተወካይ አባ ገዳዎችና ሌሎች ልዑካን ይዘው ባህርዳር ሲገቡ የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ብዙአየሁ ቢያዝንን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ተገኝተው ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
የሀገርን ህልውና እያስጠበቀ ላለው የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ ድጋፍ ለማሰባሰብ በአማራ ክልል የ“ህልውና ዘመቻ” የሚል የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው።
የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደርም የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሮችን በማካሄድ 278 ሚሊዮን ብር በጥሬ እና በዓይነት በማሰባሰብ ድጋፍ ለማድረግ አቅዶ ወደ ሥራ ገብቷል።
የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የድጋፍ አሰባሰብ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እንግዳ ዳኛው እንደገለጹት÷ ህዝብን ከአሸባሪው ህወሓት ለመጠበቅ የሚከናወኑ ተግባራት በህብረተሰቡ ሙሉ ተሳትፎ መደገፍ አለበት።
እስካሁንም አርሶ አደሩንና የንግዱን ማህበረሰብ ብቻ በማነቃነቅ 17 ሚሊየ ን 407 ሺህ ብር ድጋፍ እንደተሰበሰብ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በተመሳሳይ ለጀግናው የሀገረር ለመከላከያ ሰራዊት 2 መቶ ሺህ ብር የሚገመት ስንቅ እያዘጋጁ መሆኑን በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የሚኖሩ ሴቶች ተናግረዋል፡፡
አሸባሪው የህወሓት ቡድን የሀገሪቱ ሰላም በማደፍረሱና ሴቶችና ህጻናትን ወደ ጦርነት ማሰማራቱ እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል፡፡
የጉራጌ ዞን ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ መሰረት አመርጋ ÷ አሸባሪው የህወሓት ቡድን ህጻናት ከትምህርት ገበታቸው ነጥሎ በለጋ እድሜያቸው ለጦርነት እያሰማራቸው ነው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.