Fana: At a Speed of Life!

በተቀመጠው የሲሚንቶ ዋጋ መሰረት ግብይት በማይፈጽሙ የሲሚንቶ አከፋፋዮች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መንግስት ካስቀመጠው የሲሚንቶ ዋጋ በላይ በሚሸጡ የሲሚንቶ አከፋፋዮች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ አስታወቀ ፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በሲሚንቶ ግብይት ውስጥ ያሉ ህገ-ወጥ ደላሎችን ከገበያ ሰንሰለቱ በማስወጣት እየናረ የመጣውን የሲሚንቶ ዋጋ ለማስተካከል የመሸጫ ዋጋ በመተመን ከፋብሪካ አውጥተው የሚያከፋፍሉ የመንግስት የልማት ድርጅቶችና መመሪያውን አክብረው ለመስራት የተስማሙ የግል ነጋዴዎች ተመርጠው በቅርቡ ወደ ስራ መግባታቸውን አስታውሷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮው አላስፈላጊ የሲሚንቶ ዋጋ ንረትን በመቆጣጠርና ዋጋ በመተመን የግንባታ ዘርፉ እንዳይዳከም በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

ከፋብሪካዎች ተረክበው የሚሸጡ አከፋፋዮች የሚሸጡበት የአንድ ኩንታል ዋጋ እንደየ ርቀቱ ከ240 ብር 20 ሳንቲም እስከ 388 ብር 10 ሳንቲም እንዲሆን የተወሰነ ቢሆንም አንዳንድ አከፋፋዮች ግን ከተቀመጠው ዋጋ በላይ በመሸጥ ላይ እንደሚገኙ በተደረገ የመስክ ምልከታ ማረጋገጥ ተችሏል ብሏል ቢሮው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.