Fana: At a Speed of Life!

በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ መኖሪያ ቤት የኢፍጣር ስነ-ስርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ከኢድ እስከ ኢድ ወደ አገር ቤት “ጥሪን እና የሸዋል ኢድ በዓልን አስመልክቶ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ መኖሪያ ቤት የኢፍጣር ስነ-ስርዓት ተካሄደ።
በኢፍጣር መርሐ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሐጅ÷ ታላቁን የረመዳን ወር በመፈቃቀርና በመተዛዘን እንደፈፀምነው ሁሉ በቀጣይ በዕዝነትና ትብብር መቀጠል ይገባናል ብለዋል።
በተጨማሪም በሙስሊሙና በህዝበ ክርስቲያኑ መካከል ጥብቅ ቁርኝት መኖሩን ጠቅሰው÷̋ በሀሰት ሊከፋፍሉን የሚሞክሩ አካላትን ልናወግዝ ይገባል ብለዋል።
በሌላ በኩል ተዘግቶ የቆየው የሀጅ እና ዑምራ ጉዞ መፈቀዱንም ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር ኢድሪስ አስታውቀዋል፡፡
በዓለምሰገድ አሳዬ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.