Fana: At a Speed of Life!

በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላትና ቤተሰቦች ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላትና ቤተሰቦች ከ4 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ ድጋፍ ለተፈናቀሉ ወገኖች አበርክተዋል፡፡
በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሀገሪቱ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ባካሄዱት የበይነ መረብ ውይይት ለተፈናቀሉ ወገኖች ሰብአዊ ድጋፍ፣ መልሶ መቋቋሚያና ለደረሰው የመሰረተ ልማት ውድመት ግንባታ እንዲውል የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር በማዘጋጀት ከ2 ሚሊየን ብር በላይ አሰባሰቡ።
በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሱለይማን ደደፎ÷ ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት የዜጎቿንና የወዳጆቿን ድጋፍ እንደምትፈልግ በማንሳት ውድመት የደረሰባቸውን የልማት አውታሮችን መልሶ ለመገንባትም ኢትዮጵያውያኑ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸውን ከዳያስፖራ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላትና ቤተሰቦች ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው ቁሳቁሶችን በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ አድርገዋል።
በቢሾፍቱ ከተማ ማዘጋጃ የድጋፍ ርክክቡን ያስፈፀሙት የአየር ኃይል ኢንዶክትሪኔሽን ዳይሬክተር ኮለኔል ተሾመ በዳዳ ፥ በሠራዊቱ እና በሌሎች የጸጥታ ሀይሎች የጋራ ጥምረት በአሁን ወቅት የጁንታው ግብአተ መሬት በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የቢሾፍቱ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ አብዱልሰላም መሐመድ በበኩላቸው፥ በቀጣይም የጥፋት ቡዱኑ ለኢትዮጵያ ስጋት ወደማይሆንበት ደረጃ እስኪደርስ በሚደረገው ዘመቻ ከሠራዊቱ ጎን እንደሚቆሙ ማረጋገጣቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.