Fana: At a Speed of Life!

በቱኒዚያ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣን ተነሱ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቱኒዚያ በኮሮና ቫይረስ አያያዝ ምክንያት የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣን ተነስተዋል፡፡
የቱኒዚያ መንግስት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር የወሰደውን እርምጃ በመቃወም በርካታ ዜጎች አደባባይ በመውጣት ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡
ይህን ተከትሎም የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ካኢስ ሳኤድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሂኬም ሚቺቺን ከስልጣን ማንሳታቸው ተሰምቷል፡፡
ከዚህ ባለፈም ፕሬዚዳንቱ የሀገሪቱን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማገዳቸው ነው የተገለጸው፡፡
በአንጻሩ ተቃዋሚዎች የፕሬዚዳንቱ ውሳኔ መፈንቅለ መንግስት መሆኑን እየገለጹ ነው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.