Fana: At a Speed of Life!

በታህሳስ ወር ከ 344 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባሳለፍነው ታህሳስ ወር ብቻ ከ 344 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የተለያዩ የገቢ እና ወጪ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።
በታህሳስ ወር በተካሄደው ቅንጅታዊ የኮንትሮባንድ መከላከል ስራ ግምታዊ ዋጋቸው ብር 274ሚሊየን 708 ሺህ 289 የሆኑ የገቢ ኮንትሮባንድ ዕቃዎችና ህገወጥ ገንዘቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
በሌላ በኩል ከ 70 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የተለያዩ ወጪ የኮንትሮባንድ አይነቶች መያዛቸው ተመላክቷል፡፡
በአጠቃላይ በወሩ ብር 344 ሚሊየን 715 ሺህ 978 የሚያወጡ ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተይዘዋል፡፡
በገቢ ኮንትሮባንድ የተያዙት ዕቃዎች በተለይም በጅጅጋ፣ በሀዋሳ፣ በድሬዳዋ፣ በሞያሌና ኮምቦልቻ ቀዳሚውዎቹን ስፍራዎች የሚይዙ ሲሆን÷ በወጪ ኮንትሮባንድ ደግሞ አዲስ አበባ ኤርፖርት፣ ሃዋሳ፣ ሞያሌ፣ ጅማ እና ጅጅጋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ከፍተኛ መጠን ያለው የኮንትሮባንድ ዕቃ የያዙ ናቸው።
ወደ ውጭ ሊወጡ ሲሉ ከተያዙት እቃዎች መካከል አደንዛዥ ዕፆች፣ ህገወጥ ገንዘብ፣የተለያዩ የግብርና ምርቶች፣ ማዕድናት እና የቁም እንስሳት ሲገኙ በገቢ ኮንትሮባንድ ደግሞ ልባሽ ጨርቆች፣ ኤሌክትሮኒክሶች፣ የምግብ ምርቶች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ መድኃኒትና ሌሎችም ዕቃዎች መካተታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Boost Post
23
3 Comments
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.